languageIcon
search
search

የጠዋትና የምሽት ዚክሮች

SleepAdhkar
የመኝታ አዝካሮች

አላህ በባሪያው ላይ ከዋለው ችሮታዎች መካከል አንዱ ማንኛውም የአላህ ባሪያ እጅግ የላቀ ምንዳን ይቀዳጅ፣ ይጠበቅ፣ ይከላከል፣ የነቢዩን (የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን) አርአት ተከታይ ይሆን ዘንድ ከጠዋት አንስቶ ማታ ወደመኝታው እስኪያመራ ድረስ ዚክሮችን ከእሱ ጋር እንዲቆራኙ ማድረጉ ነው፡፡

ማመልከት
AfteroonAdhkar
የምሽት አዝካሮች

አንድ የአላህ ባሪያ ቀኑን የልእልና ባለቤት የሆነውን አላህን በማስታወስ እንዲያካብብ፣ አላህን በማውሳትም ከሰይጣኖች ጉትጎታ እንዲጠበቅ እንዲሁም ‹‹ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡›› (ቃፍ ፡ 39) ለሚለው የአላህ ቃል ምላሽ በመስጠት የነቢዩን (የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን) ፈለጎች ተምሳሌት አድርጎ እንዲከተል አላህ (ሱ.ወ) ባሪያዎቹ የጠዋት እና የምሽት አዝካሮችን እንዲሉ አነሳስቷል፡፡

ማመልከት
morningAthkar
የጠዋት ዚክሮች

ትክክለኛው ጎህ ሲቀድ አንድ ሙስሊም የዚክርና የመጠበቂያ ልብሶችን ልእልና የተገባው አላህ፤ ‹‹ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡›› በማለት የተናገረውን ለመተግባር፣ የቀን ተግባራቱ ጅማሮ እንዲሆንና በትእዛዝ ላይ የታነጸ ይሆን ዘንድ ይለብሳል፡፡

ማመልከት
talqeenRight
التلقين

በትክክል እንዲያነቡና እንዲያውቁ ማስቻል


አጫጭር የሆኑ የቁርአን ምዕራፎችንና ትክክለኛ የሆኑ አዝካሮችን ምንም ችግር በሌለበት ዘዴ እንዲያነቡ የሚያስችልዎትን የምናቀርብልዎ አገልግሎት ነው፡፡

. በተደጋጋሚ በደንብ ማጥናትንና በትክክል ቃሉን ማንበብ ለማረጋገጥ ማስቻል

. የድምጽ ፋይሎችን እጅግ ውብ የሆኑ ድምጽ ባለቸው አንባቢዎች እናቀርብልዎታለን

መማርዎትን ይጀምሩ