languageIcon
search
search

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

 أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، اللهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا فِي هَذَا الْيَوم وَخَيْر مَا بعدِه، وَأَعُوذُ بِك مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذا اليَوم وَشَر مَا بَعْدِه، اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ،  وَالْهَرَمِ، وَسُوءِ الْكِبَرِ، وَفِتْنَةِ الدُّنْيَا، وَعَذَابِ الْقَبْرِ 

አስበሕና ወአስበሐ-ልሙልኩ ሊልላህ፣ ወልሐምዱሊልላህ ላ ኢላሀ ኢልለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፣ አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ሚን ኸይሪ ሀዚ-ልየውሚ ወኸይረ ማ በዕደሁ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ሀዘል-ልውሚ ወሸርረ ማ መማዐደሁ አልላሁምመ አንኒ አዑዙ ቢከ ሚል ከሰሊ፣ ወልሀረሚ፣ ወሱኢል ኪበሪ፣ ወፊትነቲ-ድዱንያ፣ ወዐዛቢ-ልቀብር፡፡”  /አነጋን፣ ንግስናም ለአላህ ሆኖ  ነጋ፡፡ ምስጋናም አላህ ነው፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ ብጤም የለውም፡፡ አላህ ሆይ! ከዚህች ቀን መልካም ነገርንና በውስጧም ካለው መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ በመጠፎ ነገሮቿና በውስጧም ከሚገኝ መጥፎዋ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ከስንፍና፣ ከሽምግልና፣ ከመጥፎ እርጅና፣ ከምድር ፈተና እና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ፡፡/  ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2723) ዘግበውታል፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ خَلَقْتَنِي، وَأَنَا عَبْدُكَ,وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ, أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ

ሰይዪዱ-ልኢስቲግፋር (ምህረት የመጠየቂያ ቃላት የበላይ)፡- “አልላሁምመ አንተ ረብቢ ላ ኢላሀ ኢልላ አንተ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዐላ ዐህዲክ ወወዕዲክ ማስተጠዕቱ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ማሰነዕቱ አቡዉኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለይየ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈኢንነሁ ላ የግፊሩ-ዝዙኑዉበ ኢልላ አንተ፡፡ /አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፡፡ ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ የፈጠርከኝ አንተ ነህ፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ በምችለው አቅም በቃል-ኪዳንህና በቀጠሮህ ላይ ነኝ፡፡ በእኔ ላይ በለገስከው ጸጋዎችህ ወዳንተ እመለሳለሁ፡፡ በወንጀሎቼም ወዳንተ እመለሳለሁ፡፡ ወንጀሎቼን ማርልኝ፡፡ በርግጥ ካንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር ማንም የለም፡፡/” የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “እርግጠኛ ሆኖ በቀኑ ክፍለ-ጊዜ ላይ ያለና በዚያው ቀኑ ሳይመሽ የሞተ እንደሆነ እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኖ ሌሊት ላይ ያለና በዚያው ሌሊት ላይ ሳያነጋ የሞተ እንደሆነ እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6306) ላይ ዘግበውታል፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ، عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيكَهُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِي سُوءًا، أَوْ أَجُرَّهُ إِلَى مُسْلِمٍ

አልላሁምመ ፋጢሪ-ስሰማዋቲ ወልአርድ፣ ዓሊሚ-ልገይቢ ወሽሸሃደህ ላ ኢላሀ ኢልላ አንተ ረብበ ኩል ሸይኢን የመሊይከሁ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ነፍሲ ወሚን ሸርሪ-ሽሸይጣኒ ወሺርኪሂ ወአን አቅተሪፈ ዐላ ነፍሲ ሱዉአን አው አጁርረሁ ኢላ ሙስሊም፡፡ /አላህ ሆይ! የሰማያትና የምድር ፈጣሪ፣ ሩቅና ድብቅ እውቀቶችን የምታውቅ የሆነከው ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንተ የሁሉም ጌታና ገዢ ነህ፡፡ ከነፍሴ ተንኮል፣ ከሸይጣንም ተንኮልና ጉትጎታ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ በነፍሴ ላይ መጥፎ ነገርን ከምሰራ ወይም ወደሙስሊም እንዳልወስድ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡/” ይህን አስመልክተው ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ስታነጋ፣ ስታመሽ፣ መኝታህን ስትይዝ ይህችን በላት” ብለዋል፡፡ አሕመድ ሐዲሡን በሐዲሥ (6597)፣ አቡ ዳዉድ በቁጥር (5076)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (3529)፣ አን-ነሳኢይ በቁጥር (7699) ላይ ዘግበውታል፡፡ኢብን ባዝም -አላህ ይዘንላቸው- የዘገባ ሰነዱን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ 

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ، وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِي، وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي

አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ-ልዓፈየተ ፊድዱንያ ወልኣኺረህ፣ አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ አል-ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊዲይኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አልላሁምመ-ስቱር ዐውራቲ ወኣሚን ረውዓቲ፣ አልላሁምመ ኢሕፊዝኒ ሚን በይኒ የደይየ ወሚን ኸልፊ ወዐን የሚይኒ ወዐን ሺማሊ ወሚን ፈውቂ ወአዑዙ ቢዐዘመቲከ አን አግታለ ሚን ተሕቲ፡፡ /አላህ ሆይ! በሃይማኖቴና በምድራዊ ሕይወቴ ላይ ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! በሃይማኖቴ፣ በምድራዊ ሕይወቴ፣ በቤተሰቤና በገንዘቤ  ይቅርታንና ደህንነተን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ነውሬን ደብቅልኝ፡፡ ክብሬን ጠብቅልኝ፡፡ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ፣ ከበስተኋላዬ፣ በቀኜ፣ በግራዬ፣ ከላዬ ጠበቀኝ፡፡ ከሥሬም እንዳልርድ በትልቅነትህ እጠበቃለሁ፡፡/” ሐዲሡን አሕመድ ሙስነድ በተሰኘው መጽሐፋቸው በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (4785)፣ አቡ ዳዉድ በቁጥር  (5074)፣ አን-ነሳኢይ ሱነኑ-ልኩብራ  በተሰኘው መጽሐፋቸው በቁጥር (10401)፣ ኢብን ማጀህ በቁጥር (3871) ሲዘግቡ አል-ሓኪም ትክክለኛነቱን አረጋግጠዋል፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

أَصْبَحْنَا عَلَى فِطْرَةِ الْإِسْلَامِ، وَكَلِمَةِ الْإِخْلَاصِ، وَدِينِ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - وَمِلَّةِ أَبِينَا إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا, وَمَا كَانَ مِنْ الْمُشْرِكِينَ

‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሲያነጉ፣ “አስበሕና ዐላ ፊጥረቲ-ልኢስላም፣ ወከሊመቲ-ልኢኽላስ፣ ወዲኒ ነቢይዪና ሙሐምመዲን -ሰልለላሁ ዐለይሂ ወሰልለም- ወሚልለቲ አቢይና ኢብራሂይመ ሐኒይፈን ወማ ካነ ሚነ-ልሙሽሪኪይን፡፡ /በኢስላም ተፈጥሮ ላይ፣ በቅንነት ቃል፣ በነብያችን ሙሐመድ -የአላህ እዝንትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ዲን ላይና በቀጥተኛው የአባታችን መንገድ ላይ አነጋን፡፡ በእርግጥ እሳቸው አጋሪ አልነበሩም፣” ይሉ ነበር፡፡›› ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (21144፣ 15365) ላይ ዘግበውታል፡፡ ሲያመሹም፣ “አምሰይና ዐላ ፊጥረቲል-ኢስላም…/በኢስላም ተፈጥሮ ላይ አመሸን…/” ይሉ ነበር፡፡ የሐዲሡን የዘገባ ሰነድ ትክክለኛነት ኢብን ባዝ -አላህ ይዘንላቸው- አረጋግጠዋል፡፡

.......