languageIcon
search
search
brightness_1 አዛንን መከታተል

አዛንን የሚሰማ ሰው ሐይየ ዐለ-ስሰላህና ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ ከሚለው በስተቀር ሙአዚኑ እንደሚለው ማለቱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ሐይየ ዐለ-ስሰላህና ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ ላይ ግን ‹‹ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ››  ይላል፡፡ 

ዐብዱላህ ኢብን ዐምር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- “ሙአዚንን ከሰማችሁ እንደሚለው ዓይነት በሉ፡፡…” ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (384) ዘግበውታል፡፡ ከዑመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- “አንድ ሙአዚን ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ሲል አንዳችሁ “ከልቡ አላሁ አክበር አላሁ አክበር” ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አሽሀዱ አን ላኢላሀ ኢልለላህ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ሐይየ ዐለ-ስሰላህ›› ሲል (አንዳችሁ) “ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ” ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ሐይየ ዐለል-ፈላሕ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹ላ ሐውላ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለላህ ሲል (አንዳችሁ) ላ ኢላሀ ኢልለላህ›› ካለ ጀነት ገብቷል፡፡ ብለዋል፡፡ ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (385) ዘግበውታል፡፡

ለፈጅር ሰላት በማነሳሺያ ቃላት ወቅት አዛኑን የሚከታተል ሰው ሙአዚኑ እንደሚለው ‹‹አስ-ሰላቱ ኸይሩን ሚነ-ንነውም›› ይላል፡፡

brightness_1 ከአዛን በኋላ በነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ላይ ሰላዋት ማድረግ፡፡

ከዐብደላህ ኢብን ዐምር ኢብን አልዓስ (ረ.ዐ) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፣ “አንድ አዛን የሚያደርግ ሰው (ሙአዚን) አዛን ሲያደርግ ከሰማችሁ (እሱ) እንደሚለው በሉ፡፡ ከዚያ በእኔ ላይ ሰለዋት አድርጉ፡፡ በርግጥ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያደረገ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያደርግለታል፡፡ ከዚያ የላቀውን ደረጃ (ከአላህ) ጠይቁልኝ፡፡ ይህች ደረጃ ከአላህ ባሪያዎች መካከል ለአንዱ ካልሆነች በስተቀር ለማንም የተገባች አይደለችም፡፡ ስለዚህ ይህ የአላህ ባሪያ እኔ እሆን ዘንድ እሻለሁ፡፡ ይህችን የላቀች ደረጃ ለእኔ የጠየቀልኝ ሰው በእርሱ ላይ አማላጅነቷ  ተረጋገጠችለት፡፡” ሲሉ በርግጥ መሰማታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (384) ዘግበውታል፡፡

በላጭ የሆነው ሰለዋት፡- ሰላቱ አል-አብራሂሚይየህ ነው፡፡ ይኸውም፡- ‹‹አላህ ሆይ! በሙሐመድ ላይና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ እዝነት አድርግ፡፡ በኢብራሂም ላይና በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ እዝነት እንዳደረግከው ሁሉ…››