languageIcon
search
search
brightness_1 መስጂድ ውስጥ ሲገቡ ቀኝ እግርን ማስቀደም፣ ሲወጡ ደግሞ ግራ እግርን ማስቀደም

አነስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹መስጂድ ውስጥ ስትገባ በቀኝ እግርህ መጀመር፣ ስትወጣ ደግሞ በግራ እግርህ መጀመርህ ከነቢያዊ ፈለጎች መካከል ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ አል-ሐኪም በሐዲሥ ዘገባ መድብላቸው ቅጽ፡ 1 ገጽ፡ 338 ላይ ሲዘግቡ በሙስሊም የዘገባ መሰፈርትነት የሐዲሡንም ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ይህም ከኢብን ዑመር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በተላለፈው ሐዲሥ መሠረት ቡኻሪ [መስጂድም ሆነ ሌላ ሥፍራ ሲገባ በቀኝ መጀመር በሚለው ምዕራፍ ሥር ኢብን ዑመር መስጂድ ሲገቡ በቀኝ እንደሚጀምሩ፣ ሲወጡ ደግሞ በግራ እንደሚጀምሩ] አስፍረዋል፡፡ ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹የአላህ መልእከተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- በሁሉም ሁኔታዎቻቸው ላይ በቀኝ መጀመርን ይወዱ ነበር፡፡››    ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (168)፣ ሙሰሊም ደግሞ በቁጥር (268) ላይ ዘግበውታል፡፡

brightness_1 ለወንዶች በመጀመሪያው ሰልፍ ላይ መቻኮላቸው ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

ለወንዶች በመጀመሪያው ሰልፍ ላይ መቻኮላቸው ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰልፍ በላጩ የሰላት ሰልፍ   ነው፡፡ ለሴቶች በላጩ ሰልፍ ደግሞ የሰላቱ የመጨረሻ ሰልፍ ነው፡፡  

አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከወንዶች ረድፎች መካከል በላጩ ረድፍ የመጀመሪያው ነው፡፡ መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው፡፡ ከሴቶች ረድፎች መካከል በላጩ ረድፍ የመጨረሻው ነው፡፡ መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው፡፡” ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (440) ዘግበውታል፡፡   በላጩ፡- ማለት በርካታ ምንዳና ትሩፋትን የሚያስገኝ ማለት ሲሆን መጥፎዋ፡- ማለት ደግሞ ዝቅተኛ ምንዳና ትሩፋት የሚያስገኝ ማለት ነው፡፡

ይህ ሐዲሥ ወንዶችና ሴቶች ግርዶሽ በሌለበት ሁኔታ ሰላትን በሕብረት (ጀማዐህ) የሚሰግዱ ከሆነ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ለሴቶች የሰላቱ የመጨረሻ ረድፍ በላጭ ነው፡፡ ምክንያቱም ራሳቸውን ከወንድ ዓይኖች እንዲጠበቁ ምክንያት ይሆንላቸዋልና ነው፡፡  እንደግርግዳና ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት ዓይነት ግርዶሽ ያለበት ሥፍራ ወይም ልክ ለሴች መስገጃ ይሆን ዘንድ ልዩ ክፍል እንደሚዘጋጅባቸው አብዛኛዎቹ መስጂዶቻችን ዓይነት ከሆነ  ለሴቶች በላጩ ረድፍ የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህም ከወንዶች እኩል ይሆኑ ዘንድ ለማስቻል ነው፡፡ በማንኛውም የመጀመሪያ የሰላት ረድፍን አስመልከቶ የተዘገቡ ሐዲሦች በርካታ ናቸው፡፡ ከእነርሱም መካከል፡-

አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ረድፍ ውስጥ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮና እሱ ላይ እጣ ከመጣጣል በስተቀር ሌላ የማያገኙ ቢሆን እጣ ይጣጣሉ ነበር፡፡ ሰዎች በመክፈቻው ተክቢራ ውስጥ ያለውን ቢያውቁ ኖሮ ወደርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ በምሽት -በዒሻእ- እና በሱብሒ ሰላቶች ውስጥ ያለውን ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር፡፡” ብለዋል፡፡ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (615)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (437) ላይ ዘግበውታል፡፡