languageIcon
search
search
brightness_1 ነጫጭ የሆኑ ልብሶችን መልበስ ነቢያዊ ፈለግ ነው

የዚህ ርዕስ መልእክት አንድ ሰው ካሉት በተለያዩ ቀለማት የተቀለሙ ልብሶች መካከል (ነጭ) ልብስ መልበሱ ከነቢያዊ ፈለጎች መካከል አንዱ ነው የሚል ነው፡፡ ኢብን ዐብባስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከልብሶቻችሁ ነጩን ልብስ ልበሱ፡፡ በእርግጥ መልካሙ ልብሳችሁ ነው፡፡ በእርሱም ሙታኖቻችሁን ከፍኑ፡፡” ብለዋል፡፡ አሕመድ በቁጥር (2219)፣ አቡ ዳዉድ በቁጥር (3878)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (994)  የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒይ ትክክለኛነቱን ዘግበውታል፡፡ ሰሒሑ-ልጃሚዕ ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 267፡፡

ሸይኻችን ኢብን ዑሠይሚን -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ይህ ሐዲሥ እንደቀሚሶች፣ ሸርጦች፣ ሱሪዎች ያሉትን ነጭ ልብሶችን ያጠቃለለ ነው፡፡ ሁሉም ግን ነጭ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ይህ በጣም ተመራጭ ነው፡፡  ይሁን እንጂ አንድ ሰው ካሉት ልብሶች መካከል ሌላ ቀለም ያላቸውን ልብሶች ቢለብስ ምንም ችግር የለውም፡፡ የሚለብሳቸው ልብሶች ግን ለሴቶች ተብለው የተለዩ አለመሆናቸው በመስፈርተነት የተቀመጠ ነው፡፡›› ሸርሑ ረያዱ-ስሳሊሒን     ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 1087፡፡

 

brightness_1 ሽቶ መቀባት ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

አነስ -አላህ መልካም ሠራዎቻቸውን ይውደዳቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከምድራዊው ዓለም በእኔ ዘንድ ሰቶች፣ ሽቶ እጅግ የተወደዱ ተደርገውልኛል፡፡ የዓይን ማረፊያዬ በሰላት ውስጥ እንዲሁ ተደርጎልኛ፡፡” ብለዋል፡፡ አሕመድ በቁጥር (12293)፣ አን-ነሳኢይ በቁጥር (3940) የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒይ በሰሒሑ አን-ነሳኢይ ውስጥ ሐዲሡን ‹‹ሐሰኑን ሰሒሕ›› ብለዋል፡፡

ነገር ግን፣ “ከምድራዊው ዓለማችሁ በእኔ ዘንድ ሶስት ነገሮች የተወደዱ ተደርገውልኛል፡፡” የሚለው ዘገባ የሐዲሡ ደረጃ ደካማ ነው፡፡

ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከእሳቸው ላይ መጥፎ ጠረን መኖርን ይጠሉ ነበር፡፡ ቡኻሪ ከዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በዘገቡት ረዥም ሐዲሥ ውስጥ ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከእሳቸው ላይ ሽታን ማግኘት ይበረታባቸው ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹ሽታን ማግኘት ይበረታባቸው ነበር፡፡›› ማለት ጥሩ ያልሆነ ሽታን ማግኘት ማለት ነው፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6972) ላይ ዘግበውታል፡፡  

ሽቶን መመለስ ይጠላል

አነስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሽቶን አይመልሱም ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2582) ላይ ዘግበውታል፡፡