languageIcon
search
search
የጠዋትና የምሽት ዚክሮች የጠዋትና የምሽት ዚክሮች ( ቁጥሯም 4 ክፍሎች )

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

በመኝታ ወቅት አየቱ-ልኩርሲይን መቅራት ነቢያዊ ፈለግ ከመሆኑ በተጨማሪ ለሚለው ሰው እስኪያነጋ ድረስ ከሸይጣን መጠበቂያውም ነው፡፡

ለዚህ ማስረጃው፡- የአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ከዘካ ንብረት ላይ ከሚሰርቀው ጋር የነበራቸው ታሪክ ነው፡፡ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ምርኮኛህ ትናንተና ምን ሰራ?” አሉኝ፡፡ እኔም፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ በርሱ ሊጠቅመኝ የሚችልበትን ቃላት ሊያስተምረኝ ወሰነ፡፡ እንዲሄድ አደረግኩት አልኳቸው፡፡ እሳቸውም፣ “ምንድን ነች እሷ?” አሉኝ፡፡ እኔም፡- ‹‹ወደመኝታህ ከመጣህ አየቱ-ልኩርሲይን

{اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ}  አንቀጹን እስከምትጨርስ ድረስ ቅራ፡፡ ካንተ ላይ በርግጥ ከአላህ የሆነ ጠባቂ ፈጽሞ አይለይም፡፡ እስከምታነጋ ድረስም  ሸይጣን አይቀርብህም፡፡ እነርሱ በመልካም ነገር ላይ ተነሳሽ የሆኑ ናቸው፡፡›› አለኝ አልኳቸው፡፡ ነቢዩም -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “እሱ በጣም ውሸታም ሆኖ ሳለ እውነቱን ነግሮሃል፡፡ አባ ሁረይራህ ሆይ! ለሶስት ቀናት ማንን ታናግር እንደነበር ታውቃለህን?” አሉኝ፡፡ እኔም፡- ፈጽሞ አላውቅም አልኳቸው፡፡ እሳቸውም፣ “ያ ሸይጣን ነው፡፡” አሉኝ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2311) በሐዲሡ ላይ ሃሳብ ሰጥተው ሲዘግቡት አን-ነሳኢይ በአስ-ሱነኑ-ልኩበራ መጽሐፋቸው በቁጥር (10795) ላይ ዘግበውታል፡፡ 

 

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

አቢ መስዑድ አል-አንሳሪይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በአንድ ምሸት እነዚህ ሁለት አንቀጾች ከአል-በቀራህ ምዕራፍ የቀራ ከሁሉ ነገር ይብቃቁታል፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (4008)፣ ሙሰሊም ደግሞ በቁጥር (807) ላይ ዘግበውታል፡፡ ሁለቱ የአል-በቀራህ ምዕራፍ የመጨረሻ አንቀጾች በተለይ በመኝታ ላይ ከሚባሉት አዝካሮች መካከል የሚቀመጡ ሳይሆን በምሽት ላይ የሚቀሩ የቁርአን አንቀጾች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁለት አንቀጾች ምሽት ላይ ያልቀራቸውና መኝታው ላይ ያስታወሳቸው ሰው በዚያ ወቅት ይቅራቸው፡፡ 

(ይብቃቁታል) በሚለው ቃል ትርጓሜ ላይ ዑለሞች በሃሳብ ተለያይተዋል፡፡ ይኸውም፡-

ከሌሊት ሰላት ይብቃቁታል ማለት ነው የተባለ ሲሆን ከሸይጣን ይከለክሉታል   ማለት ነው ተብሏልም፡፡

እንደዚሁ ከስህተት ይከላከሉታል ተብሏል፡፡ ሁሉም እንደሚሆን አን-ነወዊይ   -አላህ ይዘንላቸው- አስፍረዋል፡፡ ሸርሑ አን-ነወዊይ ሊሙሰሊም  የአል-ፋቲሐና የአል-በቀራህ ምዕራፍ መደምደሚያዎች… በሚለው ምዕራፍ ሥር ሐዲሥ ቁጥር (808)ን ይመልከቱ፡፡

.......

3 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

ለዚህ ማስረጃው፡-

ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- በየምሽቱ ወደመኝታቸው ሲሄዱ ሁለቱን መዳፎቻቸውን ይሰበስቡና እትፍ እትፍ ይለባቸዋል፡፡ በውስጣቸውም፣

{قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ} وَ {قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ} وَ {قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ}  

ቁል ሁወ-ልላሁ አሐድ”ን፣ “ቁል አዑዉዙ ቢርብቢ-ልፈለቅ”ንና “ቁል አዑዉዙ ቢረብቢ-ንናስ”ን ይቀሩባቸዋል፡፡ ከዚያም የቻሉትን ያህል ሰውነታቸውን ያብሱባቸዋል፡፡ ከራሳቸው፣ ከፈታቸውና ከፊት ለፊት ካለው ሰውነታቸውም ማበስን ይጀምሩባቸዋል፡፡ ይህን ሶስት ጊዜ ይፈጽሙ ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (5017) ላይ ዘግበውታል፡፡

ከዚህ ካሳለፍነው ሐዲሥ የምንቀስመው፡- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ይህን ነቢያዊ ፈለግ ተግባራዊ ያደርጉ እንደነበር ነው፡፡ ይህንንም ‹‹በየምሽቱ›› ብለው ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በተናገሩት ሐዲሥ ላይ እናገኛለን፡፡ ይህን ነቢያዊ ፈለግ ይተገብሩ ነበር ማለት መዳፎቻቸውን ስብስበው ከዚያ የአል-ኢኽላስንና የአል-ሙአውዊዘተይንን ምዕራፍች ካነበቡ በኋላ እትፍ እትፍ ይሉባቸዋል ከዚያ ከራሳቸውና ከፊታቸው በመጀመር የቻሉትን የሰውነታቸውን አካል ያብሱባቸዋል፡፡ ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈጽሙ ነበር፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَاوَاتِ وَرَبَّ الأَرْضِ وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ، فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى، وَمُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالإِنْجِيلِ وَالْفُرْقَانِ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ، اللَّهُمَّ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ ، وَأَنْتَ الآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ، اقْضِعَنَّا الدَّيْنَ وَأَغْنِنَا مِنَ الْفَقْرِ

አልላሁምመ ረብበ-ስሰማዋቲ ወረብበ-ልአርዲ ወረብበ-ልዐርሺ-ልዐዚይም ረብበና ወረብበ ኩልሊ ሸይእ ፋሊቁ-ልሐብቢ ወ-ንነዋ ሙንዚለ-ትተውራቲ ወልኢንጂሊ ወልፉርቃን አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ኩልሊ አንተ ኣኺዙን ቢናሲየቲሂ አልላሁምመ አንተ-ልአውወሉ ፈለይሰ ቀብለከ ሸይኡን ወአንተ-ልኣኺሩ ፈለይሰ በዕደከ ሸይኡን ወአንተ-ዝዛሂሩ ፈለይሰ ፈውቀከ ሸይእ ወአንተ-ልባጢኑ ፈለይሰ ዱዉነከ ሸይእ ኢቅዲ ዐንና-ድደይነ አግኒና         ሚነ-ልፈቅር፡፡/የሰማያት፣ የምድር፣ የላቀው ዐርሽ ጌታ፣ ጌታችንና የሁሉም ነገር ጌታ የሆንከው፣ አንተ ፍሬንና በቆልተን ፈልቃቂ፣ ተውራትን፣ ኢንጂልንና ቁርኣንን የምታወርድ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተ አናቱን ያዥ የምትይዝ በሆንከው ባንተ ከሁሉም ነገር ተንኮል እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! አንተ የመጀመሪያው ነህ ካንተ በፊት ምንም ነገር የለም፡፡ አንተ ግልጹ ነህ ከበላይህ ምንም ነገር የለም፡፡ አንተ ስውሩ ነህ ካንተ ውጭ ምንም ነገር የለም፡፡ እዳችንን ክፈልልን፡፡ ከድህነትም አብቃቃን፡፡/” ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2713) ላይ  ዘግበውታል፡፡

.......

100 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

سبحان الله (33)، الحمد لله (33)، الله أكبر (34) م

አንድ ሰው ለመተኛ ሲፈልግ ሰላሳ ሶስት ጊዜያት ተስቢሕና ተሕሚድ (አላህም ከከንቱና ውድቅ ከሆኑ ንግግሮች ማጥራቱና አላህን ማመስገኑ) እንዲሁም ሰላሳ አራት ጊዜ ተክቢር (አላህን ማላቁ) ነቢያዊ ፈለግ ሲሆን ትሩፋቱም የላቀ ነው፡፡ ይኸውም ለሰውነት ብርታት ይሰጣል፡፡

ለዚህም ማስረጃው፡- ዐሊይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ፋጢመህ በመጅ ምክንያት እጇ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት አቤት አለች፡፡ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ወደምርኮኞች መጥተዋል፡፡ ወደእሳቸው ዘንድ አላገኘቻቸውም፡፡ ዓኢሻን አገኘች፡፡ ሁኔታውን ነገረቻት፡፡ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሲመጡ ፈጢመህ ወደእሷ ዘንድ እንደመጣች ነገረቻቸው፡፡ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- መጡ፡፡ መኝታችንን ይዘናል፡፡ ለመሳት ዳዳን፡፡ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- “በቦታችሁ ላይ ሁኑ፡፡” አሉን፡፡ የእግራቸውን ቅዝቃዜ ደረቴ ላይ እስኪሰማኝ ድረስ በመካከላችን ተቀመጡ፡፡ ከዚያም፣ “ከጠየቃችሁት የተሻለ ነገር ላስተምራቸሁን? መኝታችሁን ስትይዙ አላህን ሰላሳ አራት ጊዜ ታልቃላችሁ፣ ከከንቱና ውድቅ ከሆኑ ንግግሮች ሰላሳ ሶስት ጊዜ ታጠሩታልችሁ፡፡ ሰላሳ ሶሰት ጊዜ ታመሰግኑታላችሁ፡፡ ይኻችሁ ከአግልጋይ ለናንተ የተሻለ ነው፡፡” አሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ቁጥር (3705)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2727) ላይ ዘግበውታል፡፡

በሌላ ዘገባ ዐሊይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ከነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከሰማሁት በኋላ ፈጽሞ አልተውኩትም፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹በሰፊን ሌሊትም ቢሆን?›› ተባሉ፡፡ እሳቸውም፣‹‹በሰፊን ሌሊትም ቢሆን›› አሉ፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ቁጥር (5362)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2727) ላይ ዘግበውታል፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْلَمْتُ وَجْهِي إِلَيْكَ، وَفَوَّضْتُ أَمْرِي إِلَيْكَ، وَأَلْجَأْتُ ظَهْرِي إِلَيْكَ، رَغْبَةً وَرَهْبَةً إِلَيْكَ. لاَ مَلْجَأَ وَلاَ مَنْجَا مِنْكَ إِلاَّ إِلَيْكَ، آمَنْتُ بِكِتَابِكَ الَّذِي أَنْزَلْتَ، وَبِنَبِيِّكَ الَّذِي أَرْسَلْتَ

አልላሁምመ ኢንኒ አስለምቱ ወጅሂ ኢለይክ ወፈውድቱ አምሪ ኢለይክ፣ ወአልጀእቱ ዘህሪ ኢለይክ ረግበተን ወረህበተን ኢለይክ ላመልጀአ ወላ መንጃ መንከ ኢልላ ኢለይክ ኣመንቱ ቢኪታቢክ-ልለዚ ኣመንቱ ቢኪታቢከ-ልለዚ አንዘልት ወቢነቢይዪከ-ልለዚ አርሰልት፡፡ /አላህ ሆይ! ፊቴን ወዳንተ አሳልፌ ሰጠሁ፡፡ ጉዳዬን ወዳንተ አቤት አልኩ፡፡ ጀርባዬን ወዳንተ አስጠጋሁ፡፡ በፍላጎትና በፍራቻ ወዳንተ መጣሁ፡፡ ወዳንተው ካልሆነ በስተቀር በርግጥ መጠጊያና ካንተ መሸሺያ የለም፡፡ በዚያ ባወረድከው መጽሐፍህና በላከው ነቢይህም አመንኩ፡፡/” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (247)፣ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2710) ላይ ዘግበውታል፡፡ በሐዲሡ መጨረሻ ላይ፣ “-በምድር ላይ የመጨረሻ ንግግርህ አድርጋቸው፡፡ በዚያች ሌሊት ከሞትክ አንተ በኢስላም ላይ ሆን ሞተሃል፡፡” ያሉ ሲሆን በሌላ የሙስሊም ዘገባ፣ “ካነጋህም በመልካም ነገር ላይ አንግተሃል፡፡” ብለዋል የሚል ዘገባ ተዘግቧል፡፡

በዚህ ሐዲሥ ላይ ሌላ ነቢያዊ ፈለግ እናገኛለን፡፡ ይኸውም፡- አንድ ሰው ይህን ዚክር ከመተኛቱ በፊት የሚናገረው የመጨረሻ ንግግሩ ሊያደርገው ይገባል፡፡  ምናልባት በዚያ ሌሊት ላይ ቢሞት ትልቅ ምንዳ ይታሰብለታል፡፡ በኢስላም ተፈጥሮ ላይ ሆነው ከሞቱት ጋር ይሆናል፡፡ በሌላ አነጋገር ቀጥተኛ በሆነው በኢብራሂም -የአላህ ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ፈለግ ላይ ሞቷል፡፡ ካነጋ ደግሞ በመልካም ሲሳዩና ስራው  ላይ ሆኖ ይሞታል፡፡ ይህ አነጋገር ከዚህ በላይ ካለፉት ሁሉ የተሻለና ሁሉንም ነገሮች ያጠቃለለ ነው፡፡ -አላህ ይበልጥ ዐዋቂ ነው-፡፡

.......

1 በርካታ ጊዜያት

brightness_1

اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ

በዚህ ላይ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው ነገር ቢሆን፡- ይህ አላህ የክብርና የልእልና ባለቤት የሆነው ጌታ የተመጻደቀበት የሆነ በእጅጉ የላቀ ዚክር ነው፡፡ የትልቅ ትሩፋት ሰበብም ነው፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ከሸድዳድ ኢብን አውስ      -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በዘገቡት ሐዲሥ ነቢዩ         -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “የኢስቲግፋር የበላይ ማለት፡- አልላሁምመ አንተ ርብቢ ላ ኢላሀ ኢልላ አንተ ኸለቅተኒ ወአና ዐብዱከ ወአና ዐላ ዐህዲክ ወወዕዲክ መ-ስተጠዕቱ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ማ ሰንዕቱ አቡዉኡ ለከ ቢኒዕመቲከ-ልለቲ ዐለይየ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈ ኢንነሁ ላየግፊሩ-ዝዙኑበ ኢልላ አንተ/አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንተ ፈጥረኸኛል፡፡ እኔ ባሪይህ ነን፡፡ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል-ኪዳንህና በቀጠሮች ላይ ነኝ፡፡ ከፈጸምኩት ተንኮል ባንተ እጠበቃለሁ፡፡በኔ ላይ ባጎናጸፍከው ጸገዎችህ ወዳንተ እመለሳለሁ፡፡ በወንጀሌም ወዳንተ እመለሳለሁ ወንጀሌን ማርልኝ፡፡ በእርግጥ ካንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር የለም፡፡/ ማለትህ ነው፡፡ እውነት ነው ብሎ ያለ ከማምሸቱ በፊት በዚያ ቀኑ ከሞተ እሱ ከጀነት ሰዎች መካከል ነው፡፡ ሌሊት ላይ እውነት ነው ብሎ ያለ ሳያነጋ በፊት ከሞተ እሱ ከጀነት ሰዎች መካከል ነው፡፡” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6306) ላይ ዘግበውታል፡፡

 

.......