languageIcon
search
search
brightness_1 ከማፋሸግ ነቢያዊ ፈለጎች መካከል ማፋሸጉን መደበቅ ወይም በእጅ መመለስ ነው፡፡

ለዚህ ማስረጃው፡-

አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “”የሚያነጥሱ ሰዎችን አላህ ይወዳል፡፡ ማፋሸግንም ይጠላል፡፡ አንድ ሰው አነጥሶት አላህን ካመሰገነ ሲያስነጥስ በሰሙት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ አላህ ይማርህ የማለት ግደታ አለባቸው፡፡ ማፋሸግ ግን በርግጥ እሱ ከሸይጣን ነው፡፡ በተቻለው አቅም ይመልሰው፡፡ ሰውየው፣ ‹ሃ...ህ› ካለ ሸይጣን በእሱ ይስቃል፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2663) ላይ ዘግበውታል፡፡

ሙስሊም  ከአቢ ሰዒድ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-በዘገቡት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንዳችሁ ካፋገ አፉን በእጁ ይያዝ፡፡ በርግጥ ሸይጣን ይገባልና ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2995) ላይ ዘግበውታል፡፡ ማፋሸግን መደበቅ አፍን በመዝጋት ይህም አፍ እንዳይከፈት በማድረግ ወይም ከንፈርን በጥርሶች አጥብቆ በመያዝ ወይም እጅን አፍ ላይ በማድረግ ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት ሊፈጸም ይችላል፡፡